Posts

Showing posts from 2017

Federalism as a tool for accomodation of ethinc diversity in Hawassa city

ምንጭ Abstract The existing ethnic federal arrangement of the  Federal democratic republic of Ethiopia (FDRE) is devised with the aim to accommodate the interests of distinct ethnic groups in Ethiopia. This paper attempted to conceptualize federalism as a tool for ethnic diversity accommodation through reviewing the existing literatures on federalism, FDRE and south regional state constitution, city proclamations, and primary data from interview made and with researchers' interpretive arguments. The finding reveals that federalism at city government status contributes to accommodate rights, interests, needs and claims of competing ethnic groups, especially of ethnic minorities better at kebele institutional structures than at city institutional structures. At city institutional structures the indigenous groups are better protected rather than the non indigenous groups. Hence, the success of this process highly depends on the mechanisms adopted for shar

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በአየር ንብረት ለውጥና በምግብ ዋስትና ላይ ያተኮረ የምርምርና የትምህርት መርሀ ግብር መጀመሩን አስታወቀ

Image
 የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከጀርመኑ ሆኸንየም ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በአየር ንብረት ለውጥና በምግብ ዋስትና ላይ ያተኮረ የምርምርና የድህረ ምረቃ ትምህርት መርሃ ግብር መጀመሩን አስታወቀ፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ በምግብ ዋስትና ላይ በሚያሳድረው ተጽዕኖና መፍትሄዎች ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው፡፡ የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ተስፋዬ አበበ እንደገለጹት፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየተደረገ ያለው ጥረት በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ተግዳሮት እየገጠመው ነው። "ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ሰፊ ጥናትና ምርምር ማድረግና በዘርፉ የተማረ የሰው ኃይል ማፍራት ያስፈልጋል" ብለዋል። ለእዚህም የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከጀርመኑ ሆኸንየም ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የአየር ንብረት ለውጥ በምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ላይ እያሳደረ ያለውን ተፅዕኖ ለመፍታት የሚያስችል ፕሮጀክት ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። እንደ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ገለጻ በፕሮጀክቱ 14 የምርምር ሥራዎች የሚካሄዱ ሲሆን በዩኒቨርሲቲዎቹ 12 ባለሙያዎች የዶክትሬት ዲግሪ ትምህርት እየተከታተሉ ይገኛሉ። በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ዶክተር ስንታየሁ ይግረም በበኩላቸው ፕሮጀክቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ በ2030 ከተያዙ 17 ዘላቂ የልማት አጀንዳዎች መካከል ሰባቱን ለማሳካት የተቀረጸ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ፕሮጀክቱ በምግብ ዋስትና፣ በአየር ንብረት ለውጥና በትምህርት ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን የገለፁት አስተባባሪው በጀርመን መንግስት በተመደበ በጀት ተግባራዊ እንደሚደረግ ተናግረዋል። በጀርመን ሆኸንየም ዩኒቨርሲቲ በአየር ሁኔታ ትንበያ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን እየሰሩ ያሉት

በሲዳማ ዞን በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች መያዛቸው ተገለጸ

Image
በደቡብ ክልል በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደቡብ ክልል በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ። በቁጥጥር ስር የዋሉትም 10 የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች፣ ሁለት ቦምቦች እና 600 ጥይቶች ናቸው። ከዚህ በተጨማሪም 3 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ቡና በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል። ፎቶ ከ ደህረ ገጽ የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መረጃ ኢንተለጀንስ ዳይሬክተር ኮማንደር ጉራማይሌ ጉራኦ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ የክልሉ ፖሊስ ባደረገው ክትትል ነው መሳሪያዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት። የጦር መሳሪያዎቹ በህገ ወጥ መንገድ ከደቡብ ሱዳን ጠረፍ የገቡና በሲዳማ ዞን ሲዘዋወሩ በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ኮማንደር ጉራማይሌ ገልፀዋል። በተጨማሪም በቤንች ማጂ ዞን በከፋ እና በሸካ ዞኖች በ10 አይሱዙ ተሽከርካሪዎች ተጭኖ፥ በህገ ወጥ መንገድ በመዘዋወር ላይ የነበረ 3 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት ቡና  በቁጥጥር ስር ውሎ ለመንግስት ገቢ መደረጉን አስታውቀዋል። ቡናውን ጭነው የነበሩ 12 አሽከርካሪዎች እና ረዳቶች ጉዳያቸው በህግ እየተጣራ እንደሚገኝም ኮማንደር ጉራማይሌ አስታውቀዋል። እንደ ኮማንደር ጉራማይሌ ገለጻ፥ በሩብ ዓመቱ በክልሉ ከ4 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ ቶርሽን ጫማዎች፣ የሞተር ሳይክል እና የመኪና ሞተር መለዋወጫዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች እንዲሁም አዲስና ልባሽ ጨርቆች መያዛቸውን ተናግረዋል። የኮንትሮባንድ እቃውን ጭነው በህገ ወጥ መንገድ ሲያጓጉዙ የነበሩ አሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው ኮማንደር ጉራማይሌ የገለፁት።