የሐዋሳ ምዕራፍ ሁለትና የሌሎች ፓርኮች ግንባታ በስድስት ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል ተባለ
ሙሉ ዜናውን ከ ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ያንቡ በሐዋሳ ከተማ በ300 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የተንጣለለው የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ፣ ለማምረቻ የተገነቡት 37 የማምረቻ ሼዶች ሙሉ በሙሉ በውጭና በአገር ውስጥ ባለሀብቶች መያዛቸው ተገለጸ፡፡ ከቀናት በኋላም በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ተመርቆ በይፋ ሥራ እንደሚጀምር ታውቋል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ አማካሪ ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ፣ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ያልቃል ተብሎ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ከክረምቱ ወራት በፊት ሊጠናቀቅ ቀናት ቀርተውታል፡፡ በመሆኑም ሰኔ 23 ቀን 2008 ዓ.ም. የግንባታ ሥራው ሙሉ ለሙሉ እንደሚጠናቀቅ ዶ/ር አርከበ ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፍጹም አረጋ በበኩላቸው እንደገለጹት፣ ከውጭ ከመጡት አሥር ዋና ዋና ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በተጨማሪ ስምንት የአገር ውስጥ ኩባንያዎች በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የማምረቻ ሼዶችን ተረክበዋል፡፡ እስካሁን ስድስት ያህል እንደነበሩ ሲገለጽ ቢቆይም፣ አቶ ፍጹም ግን ስምንት እንደደረሱና በጠቅላላው በአገሪቱ እየተገነቡ በሚገኙት ፓርኮች ውስጥ የማምረቻ ቦታ ለመከራየት የሚጠባበቁት የአገር ውስጥ ኩባንያዎች ቁጥር 22 መድረሱን ለሪፖርተር በሰጡት ማብራሪያ ጠቅሰዋል፡፡ ከዚህ ባሻገር በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ በአምራችነት ለመሳተፍ በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የማምረቻ ቦታ የተከራየው የአሜሪካው ግዙፍ የአልባሳት አምራች ፒቪኤች (ዘ ፊሊፕ ቫን ሂውዝን ኮርፖሬሽን) ከሌላኛው የአሜሪካ ቪኤች (ቫኒቲ ፌር ኮርፖሬሽን) ከስዊድኑ ኤችኤንድኤም (ሔንስ ኤንድ ማውሪትዝ ኤቢ) ኩባንያዎች ከመንግሥት ጋር በመተባበር ባዘጋጁት ጉባዔ ላይ 35 ያህል የውጭ ኢንቨስተ