12 ፓርቲዎች መጪውን ሀገራዊ ምርጫ በተመለከተ ቅሬታዎቻቸውን በጋራ ለምርጫ ቦርድ አቀረቡ
በ2005 ዓ.ም በትብብር ሲሰሩ የቆዩ 12 ፓርቲዎች ከአሁን ቀደም የጠየቅናቸው ጥያቄዎች ባልተመለሱበት ሁኔታና አሁንም ከአሁን ቀደም የተነሱትን ጥያቄዎች የሚያጠናክሩ ተግባራት እየተፈጸሙ በመሆኑ ከሀገራዊ ምርጫው በፊት ሊፈቱ ይገባቸዋል ያሏቸው ጉዳዮችን በተመለከተ ምርጫ ቦርድም ኃላፊነቱን እንዲወጣ በጋራ በጻፉት ደብዳቤ ጠየቁ፡፡ ፓርቲዎቹ ጥቅምት 5 ቀን 2007 ዓ.ም. በጻፉትና ዛሬ ለቦረወዱ ባስገቡት ደብዳቤ ላይ እንዳመለከቱት በመንግስት/ገዢው ፓርቲ በማንአለብኝነት የተወሰዱ ህገ-ወጥ እርምጃዎች ዘላቂ ልማትና ሠላም፣ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ግንባታ፣ ህገ-መንግስታዊ፣ ሰብዐዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች አከባበርና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እና ሌሎች ጉዳዮችን የተመለከቱ ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡ ፓርቲዎቹ በጋራ ካነሷቸው ጥያቄዎች መካከል፡- 1ኛ/ በተለያየ የመዋቅር ደረጃ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን ማስፈራራት፣ የአካላዊና የንብረት ጉዳት ማድረስ፣ በሃሰት ውንጀላና የፈጠራ ክስ ማሰር፣ እየተጠናከረ መምጣትና በዚህም የፓርቲዎችን በዕቅዳቸው መሰረት የመሥራትና የዕለት ተዕለት ነጻ ህጋዊ እንቅስቃሴ መገደብ፤ 2ኛ/ በአንድ በኩል የሠላማዊ ትግል ስልቶች ተግባራዊ የሚሆኑበትን መንገድ በመዝጋት፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ከህዝብ ጋር እዳይገናኙና ዓላማቸውን፣ ፕሮግራማቸውንና አማራጭ ፖሊሲዎቻቸውን ለህዝብ እንዳያደርሱ በማድረግ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ገዢው ፓርቲ ከምርጫ የጊዜ ሰሌዳ በፊት በመንግሥት መገናኛ ብዙኃን፣ መንግስታዊ መዋቅርና ሃብት በመጠቀም ለት ተለት በአብዮታዊ ዴሞክራሲ እየጠመቀ የምርጫ ቅስቀሳ ያደረገበትና እያደረገ ያለበት ሁኔታ ግልጽ መሆኑ፤ 3ኛ/ ገዢው ፓርቲ ከመንግስት ካዝና በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ተቀብሎ ያለምንም መስፈርት ለሚፈ