ሲዳማን ጨምሮ በአንዳንድ የአገሪቱ አካባቢዎች በመጪዎቹ አስር ቀናት ከባድ ዝናብ ሊያጋጥም እንደሚችል ተጠቆመ

በመጭዎቹ አስርት ቀናት በአንዳንድ የአገርቱ አካባቢዎች ከባድ ዝናብ ሊያጋጥም እንደሚችል የብሔራዊ ሜቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ አስታወቀ።
ዝናቡ በገደላማ ቦታዎች ላይ የመሬት መንሸራተትና ጎርፍ ሊያስከትል ስለሚችል ጥንቃቄ እንዲደረግም አሳስቧል።
አርሶ አደሮች ውሃ ማሳ ላይ እንዳይተኛ ቦይ ከማውጣትና ከማንጠፈፍ በተጨማሪ የተዘራና ለዘር የተዘጋጀ ማሳ በጎርፍ እንዳይሸረሸር የጎርፍ መከላከል ስራ መስራት እንደሚገባ ኤጀንሲው ገልጿል።
ፎቶ ከኮሊኢሜጂስ
በተለያዩ የአገርቱ ክፍሎች ዝናቡ ቀጣይነት ስለሚኖረው የመኸር አብቃይ አካባቢዎች የመካከለኛ ጊዜ ሰብሎችን ለመዝራት፣በቡቃያ ደረጃ ለሚገኙና የቋሚ ሰብሎችን የውሃ ፍላጎት ለመሟላት አመቺ  ነው ተብሏል።
በአፋርና ሰሜን ሶማሌ ለሚገኙ አርሶና ከፊል አርብቶ አደሮች ለመጠጥ ውሃና ለግጦሽ ሳር አቅርቦት የጎላ ጠቀሜታ እንዳለውና አርሶ አደሮች  ግብአቶችን በወቅቱ በመጠቀም  ሰብሎችን በፍጥነት መዝራት ይኖርባቸዋልም ብሏል።
እንደ ኤጀንሲው መረጃ ከኦሮሚያ ክልል ምሥራቅና ምዕራብ ወለጋ ፣ጅማ ፣ኢሉ አባቦራ፣ምዕራብና ሰሜን ሸዋ ፣አዲስ አበባ መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ  ያገኛሉ።
የጋምቤላ ክልል ዞን 1፣2 እና 4 እንዲሁም ከአማራ ክልል ምዕራብ እና ምሥራቅ ጎጃም፣ሰሜን ሸዋ ፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ባህርዳር ዙሪያ ፣አገው ፣አዊ፣ የሰሜንና የደቡብ ጎንደር ዞኖች መደበኛና ከመደበኛ  በላይ ዝናብ የሚያገኙ ናቸው።
ቤንሻንጉል ጉሙዝ ፣ ሁሉም የትግራይ ዞኖች ፣የአፋር ክልል ዞን 3፣4 እና 5 እንዲሁም ከደቡብ ክልል የሃዲያና ጉራጌ ዞኖች ፣የወላይታና የሲዳማ ዞኖች መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ የሚያገኙ ስፍራዎች መሆናቸው ተገልጿል።
ምዕራብና ምሥራቅ ሐረርጌ ፣የአርሲና ባሌ ዞኖች ፣ከፋና ቤንች ማጂ ፣ከሶማሌ ክልል ጅግጅጋ እና ሲቲ ዞን እንዲሁም ድሬዳዋ እና ሀረሪ ከመደበኛ ጋር የተቀራረበ ዝናብ ያገኛሉ።
የተቀሩት የአገርቱ አካባቢዎች በአብዛኛው ደረቃማ የአየር ሁኔታ አመዝኖባቸው እንደሚቆይ መረጃው አመልክቷል።
ምንጭ ኢዜኣ

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር