ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የሞጆ ሐዋሳ የፍጥነት መንገድ አካል ለሆነው የዝዋይ - አርሲ ነገሌ መንገድ ግንባታ ኮንትራክተሮች እንዲወዳደሩ ጨረታ አወጣ

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የሞጆ ሐዋሳ የፍጥነት መንገድ አካል ለሆነው የዝዋይ - አርሲ ነገሌ መንገድ ግንባታ ኮንትራክተሮች እንዲወዳደሩ ጨረታ አወጣ፡፡

ባለሥልጣኑ ጨረታውን ያወጣው ሐምሌ 15 ቀን 2008 ዓ.ም. ሲሆን፣ በፕሮጀክቱ ላይ ፍላጎት ያላቸው ኩባንያዎች እ.ኤ.አ. እስከ ኦክቶበር 25 ቀን 2016 ድረስ ለፕሮጀክቱ ግንባታ የሚያቀርቡትን የገንዘብ ፍላጎት ሰነድ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ለመወዳደር የሚፈልጉ ኩባንያዎች የገንዘብ ፍላጎት ሰነዳቸውን በሚያስገቡበት ጊዜ፣ 500 ሺሕ ዶላር የጨረታ ማስረከቢያ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

202 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የሞጆ - ሐዋሳ የፍጥነት መንገድ አካል ሲሆን፣ ከዝዋይ (ባቱ) አርሲ ነገሌ ያለው መንገድ ርዝመት 57.1 ኪሎ ሜትር እንደሆነ ፕሮጀክቱን በገንዘብ ከሚደግፈው የዓለም ባንክ ድረ ገጽ ለመረዳት ተችሏል፡፡

በአጠቃላይ ከሞጆ - ሐዋሳ የሚዘረጋው የፍጥነት መንገድ ከሐዋሳ - ሞያሌ በመቀጠልም ከሞያሌ - ናይሮቢ ሞምባሳ ወደብ የሚዘልቅና ኢትዮጵያን በኬንያ በኩል ከወደብ የሚያገናኝ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

የዚህ ፕሮጀክት የመጀመርያ ምዕራፍ ከሞጆ - መቂ የሚገነባው 56.8 ኪሎ ሜትር መንገድ ሲሆን፣ የቻይናው ቻይና ሬልዌይ ሰቭንዝ ግሩፕ ውል ተፈራርሟል፡፡ ኩባንያው ፕሮጀክቱን በ3.66 ቢሊዮን ብር እንደሚገነባና በ42 ወራት እንደሚያስረክብ ይጠበቃል፡፡

ሁለተኛው ምዕራፍ ከመቂ - ባቱ የሚገነባው 37 ኪሎ ሜትር መንገድ ሲሆን፣ የኮሪያ መንግሥት ባቀረበው 82 ሚሊዮን ዶላር ብድር የሚገነባ ነው፡፡ ለግንባታውም የተመረጠው ዳዎ ኢንጂነሪንግና ኮንስትራክሽን ኩባንያ ነው፡፡

የሦስተኛው ምዕራፍ ከባቱ - አርሲ ነገሌ ለሚገነባውና በአሁኑ ወቅት ጨረታው ለወጣው መንገድ ግንባታ የዓለም ባንክ 370 ሚሊዮን ዶላር ብድር አቅርቧል፡፡

http://ethiopianreporter.com/content/ለሦስተኛው-የሞጆ-ሐዋሳ-የፍጥነት-መንገድ-ግንባታ-ጨረታ-ወጣ

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር