የሐዋሳውን መሬት መንቀጥቀጥ ሽሽት ወደ አዲስ አበባ ሲጓዙ የነበሩ 5 ተማሪዎች በመኪና አደጋ ሕይወታቸው ተቀጠፈ



(ዘ-ሐበሻ) በሐዋሳ ከተማ ዛሬም እንደአዲስ የመሬት መንቀጥቀጥ ደረሰ:: ባለፈው ሳምንት ለ6 ጊዜያት የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ በርካቶችን ቤታቸው ገብተው ለማረፍ እንኳ ፍርሃት እንዲደርስባቸው አድርጎ ነበር:: የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎች የ እረፍት ጊዜ ሰጥቶ ከየቤተሰባቸው ጋር እንዲያሳልፉ ፈቃድ በሰጠው መሰረት በርካታ ተማሪዎች ወደየ ከተማቸው ያመሩ ሲሆን በዚህም መሠረት ዛሬ ከሐዋሳ ተሳፍረው ወደ አዲስ አበባ ሲጓዙ የነበሩ 5 ወጣት ተማሪዎች ሕይወታቸው በመኪና አደጋ ተቀጥፏል::
ተማሪዎቹን ከሐዋሳ ጭና ስትሄድ የነበረችው መኪና ከአዲስ አበባ ወደ ሃዋሳ ሲጓዝ ከነበረ አይሱዙ መኪና ጋር በመጋጨቷ የ5ቱ ተማሪዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ የሰጠው መግለጫ ያስረዳል:: የአደጋው መን ስ ኤ ይበልጥ እየተጣራ መሆኑንም ፖሊስ አስታውቋል::

ተሽከርካሪዋ ከአዲስ አበባ ወደ ሀዋሳ ሲጓዝ ከነበረ ኤፍ ኤስ አር አይሱዙ የጭነት መኪና ጋር በመጋጨቷ ነው አደጋው የደረሰው።
ይህ አሰቃቂ ዛሬ ጃንዋሪ 29, 2016 7 ሰዓት ላይ የደረሰው በሞጆ እና በመኪ ከተሞች መካከል ላይ በሚገኘው የአዋሽ ወንዝ ድልድይ ላይ መሆኑም ታውቋል::

ይህ የአዋሽ ድልድይ በጣም ጠባብ ከመሆኑ የተነሳ በተቃራኒ መንገድ 2 መኪኖች በአንድ ላይ ለመጓዝ አስቸጋሪ እና አስፈሪ ነው የሚሉት ለዘ-ሐበሻ አስተያየታቸውን የሰጡ የአካባቢው ነዋሪዎች የክልሉ የትራፊክ ፖሊስ በድልድዩ ላይ በአንድ ጊዜ አንድ መኪና ብቻ እንዲያልፍ የሚያዝ ህግ ማውጣት ነበረበት እንዲሁም መኪኖችም በፍጥነት እንዳይሄዱ  ማስጠንቀቂያዎችን በአካባቢው መለጠፍ ነበረበት ሲሉ ይናገራሉ::

Source http://www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2016/01/Awash-Bridge-and-hawasa-students.jpg

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር