ኢህኣዴግ የድርጅቱን ከፍተኛ ኣመራሮች መረጠ፤ ኣዲስ ፊት የለም

ሰሞኑን በመቀሌ ከተማ ሲካሄድ የሰነበተው 10ኛ  የኢህኣዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ የፓርቲውን ከፍተኛ ኣመራሮች በመምረጥ የተጠናቀቀ ሲሆን፤ ድርጅቱ በመከተል ላይ ባለው የመተካካት ፖሊሲ መስረት ኣዳዲስ የፓርቲው መርዎች ብጠበቁም ኣዲስ ፍት ሳይታይ ቀርቷል።

ፎቶ ከፋና ድረገጽ
ዝርዝር ወሬው ያፋና ነው፦
(ኤፍ.ቢ.ሲ) ካለፈው አርብ ጀምሮ 10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤውን በመቀሌ ሲያካሂድ የቆየው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኢህአዴግ/ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝን የግንባሩ ሊቀመንበር በማድረግ በድጋሚ መርጧል።
ድርጅቱ አቶ ደመቀ መኮንንን ደግሞ በምክትል ሊቀመንበርነት መርጧል።
አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ መስከረም ወር 2005 ዓመተ ምህረት በተካሄደው የኢህአዴግ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ለመጀመሪያ ጊዜ በሊቀመንበርነት መመረጣቸው ይታወሳል።
ዛሬም 180 አባላት ያሉት የኢህአዴግ ምክር ቤት አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝን በድጋሚ ግንባሩን ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ተኩል ግንባሩን በሊቀመንበርነት እንዲመሩ መርጧል።
አቶ ሀይለማርያም ባለፈው ሳምንት በሀዋሳ በተካሄደው የኢህአዴግ አባል ድርጅት በሆነው የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/ የንቅናቄው ሊቀመንበር አድርጎ እንደመረጣቸው ይታወቃል።
እንዲሁም የድርጅቱ የኦዲት እና ቁጥጥር ኮሚሽን አባላት እና አመራሮች ተሰይመዋል።
10ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ባለ ዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣትም ተጠናቋል።
ጉባኤተኞቹ በአገሪቱ የተጀመረውን ፈጣን እድገት ከህዝቡ ጋር በመሆን ለማስቀጠል ቃል ገብተዋል በመግለጫቸው።
የመልካም አስተዳደር ችግርን ለመፍታትም የሞት ሽረት ትግል እናደርጋለን ብለዋል።
የኢህአዴግ ሊቀመንበር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ የጉባኤውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ባሰሙት የመዝጊያ ንግግር የጉባኤው ተሳታፊዎች ወደየመጡበት ሲመለሱ ፈጥነው ወደ ስራ በመግባት የህዝብን አደራ ለመወጣት እንዲሰሩ አሳስበዋል።
መላው የድርጅቱ አመራር እና አባል የጉባኤውን ውሳኔ ከልብ ተቀብሎ ወደ ስራ እንዲገባም ነው የጠየቁት።
የኢህአዴግ መስመር የተመሰረተው በህዝብ ተሳትፎ ነው ያሉት አቶ ሀይለማርያም፥ ህዝቡም ይህን ተርድቶ ለጉባኤው ውሳኔዎች ስኬት ድጋፉን እንዲሰጥ ጠይቀዋል።
በምርጫ 2007 ከኢህአዴግ ጋር የተፎካከሩ በአገሪቱ የሚገኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች፥ በህጋዊ እና በሰላማዊ መንገድ ለመስራት በፈለጉት ልክ ኢህአዴግ አብሯቸው ለመስራት ዝግጁ መሆኑንም ሊቀመንበሩ አረጋግጠዋል።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው የጉባኤው ተሳታፊዎች ድርጅታዊ ጉባኤው በአራት ቀናት ቆይታው በጉዳዮች ላይ በጥልቀት እና በግልፅነት ውይይት የተደረገበት እና ለቀጣይ ጊዜ ጠቃሚ ውሳኔዎች የተላለፉበት መሆኑን ገልፀዋል።
ቀጣዩን የኢህአዴግ 11ኛ ድርጅታዊ ጉባኤን አስተናጋጅ ተረኛ ደኢህዴን በመሆኑ በሀዋሳ እንደሚካሄድ ነው ተገልጿል ።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር