በሁለት ክፍለ ከተሞቿ ሲትጋይ ያደረችው ሐዋሳ እና ጥያቄ ውስጥ የገባው የከተማ ኣስተዳደር የእሳት ኣደጋን ለመቆጣጠር ያለው ዝግጅትና ብቃት

ፎቶ ከ ተፈሪ ታደሰ

  • በከተማ ታሪክ ከፍተኛ በተባለው በዚህ የእሳት ኣደጋ በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል፤
  • ኣላሙራ ኣዲሱ ገበያ ሙሉ በሙሉ ወድሟል፤
  • በተመሳሳይ ምሽት በቱላ ክፍለ ከተማም ሁለት ቤቶች በቃጠሎው ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ታውቋል፤
  • የከተማዋ ኣስተዳደር መሰል የእሳት ኣደጋዎችን ለመቆጣጠር ያለው ዝግጅትና ብቃት ጥያቄ ውስጥ ገብቷል፤

በሲዳማዋ መዲና ሐዋሳ ከተማ በሁለት ክፍለ ከተሞቿ በተነሱ የእሳት ኣደጋዎች በሰው፤ በእንስሳት እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል። የእሳት ኣደጋ የደረሰው በኣላሙራ ኣዲሱ ገበያ እና በቱላ ክፍለ ከተማ ነው።

የወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ የኣይን እማኞችን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ በታቦር ክፍለ ከተማ ፉራ ቀበሌ በሚገኘው በተለምዶ ኣዲሱ ገበያ ተብሎ በምጠራው ስፍራ ላይ ባለፈው ቅዳሜ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ የተነሳው የእሳት አደጋ ገበያውን ሙሉ በሙሉ አውድሟል።

ባልታወቀ ምክንያት በተከሰተውና ከሰዓታት በቆየው የእሳት ቃጠሎ አንድ የአንድ አመት ከስድስት ወር ህጻን ልጅ ህይወቱ ሲያልፍ በአንድ አዛውንት ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል የመንግስት ዜና ኣውታሮች የዘገቡ ቢሆንም ከተለያዩ ምንጭ የተገኙ መረጃዎች የጉዳት መጠን ከፍተኛ መሆኑን ያመለክታሉ፡፡
የእሳት ቃጠሎውን ለማጥፋት የሀዋሳ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የእሳት አደጋ መከላከያ ብርጌድ፣ የሀዋሳ ጨርቃ ጨርቅና የሻሸመኔ ከተማ እሳት አደጋ መከላከያና የክልሉ ልዩ ሀይል ፖሊስ እሳት አደጋ መከላከያ እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች የተሳተፉ ሲሆን፤ የከተማው ኣስተዳደር መሰል ኣደጋዎችን ለመቆጣጠ ያለው ዝግጁነት እና ብቃት ኣነስተኛ መሆኑ ለጉዳቱ መባባስ ምክንያት መሆኑ ታውቋል።
በተጨማሪም ትናንት ሌሊት 8 ሰዓት ላይ በከተማው ቱላ ክፍለ ከተማ በተከሰተ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ሁለት ቤቶች በቃጠሎው ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና ያስረዳል።

ወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ በደረሰው የህይወትና የንብረት ውድመት የተሰማውን ልባዊ ሐዘን በዚህ ኣጋጣሚ ይገልጻል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር