ሲኣን/ መድረክ የጠራው ታላቅ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በሃዋሳ ከተማ ተካሄደ
ዛሬ ከቀኑ ሶስት ሰዓት ላይ ከወልደኣማኑኤል ዱባሌ ሐውልት የተሰባሰበው ሰላማዊ ሰልፈኛ በኣቶቴ እንድሁም በየሙሉ ወንጌል በተክርስቲያን በኩል ኣድርጎ ወደ መናሃሪያ በመትመም መጨረሻውን ከሃዋሳ መስቀል ኣደባባይ ኣድርጓል።
ሪፖተራችን ጥቻ ወራና እንደዘጋበው በሰላማዊ ሰልፉ ላይ በሺዎች የምቆጠሩ ሰዎች የተገኙ ሲሆን የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች ይፈቱ፤ በልማት ስም ህዝብን ማንገላታት ይቁም፤ የኣገራችን የፖለቲካ ችግሮች በድርድር እንጂ በኃይል ኣይፈቱም የምሉ መፎክሮችን ኣስምተዋል።
በሰልፉ ላይ ተጋባዥ እንግዶችን እና የመድረክ/ ሲኣን ከፍተኛ ኣመራሮች ተገኝተው ለህዝብ የተለያዩ መልዕክቶችን ያስተላለፉ ሲሆን፤ ሰላማዊ ሰልፉ በፍጽም ሰላማዊ መሆነ ሁኔታ ያለምንም ችግር መጠናቀቁን ሪፖርተራችን ጥቻ ወራና ከሃዋሳ ዘግቧል።
Comments
Post a Comment