የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ መልካም እድል ለሲዳማ ልጆች

New

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 28 (ኤፍ ቢ ሲ) የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የተማሪዎች ውጤት ይፋ ሆኗል።

ከዛሬ ጀምሮ በኢንተርኔት ድረ ገጽ www.nae.gov.et መመልከት እንደሚችሉ የሀገር አቀፈ ፈተናዎች ኤጀንሲ ለፋና በሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አስታውቋል።

የተማሪዎች ውጤት በቀጣይ 10 ቀናት ውስጥ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል የሚሰራጭ ሲሆን ፥ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም እና የመሰናዶ መግቢያ ውጤትም በቀጣይ ሁለት ቀናት ይፋ እንደሚሆን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገብረእግዚአብሄር ተናግረዋል።

በዘንድሮው አመት ፈተናውን የወሰዱ የመደበኛ ተማሪዎች ቁጥር 519,948 ሲሆኑ ከእነዚህም ውስጥ 283,712 ወንድ እና 236, 236 ሴቶች ናቸው።

የዚህን ዓመት የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን ስንመለከትም ፥ 67 ነጥብ 23 በመቶ የሚሆኑ መደበኛ ተማሪዎች ከ2 ነጥብ በላይ አስመዝግበዋል።


ፈተናውን ከወሰዱ ተፈታኞች ውስጥ 1 ነጥብ 7 በመቶ የሚሆኑት 8 ሺህ 849 ተማሪዎች 4 ነጥብ ማምጣት የቻሉ ናቸው ተብሏል።

ከእነዚህም ውስጥ 6 ሺህ 441 የሚሆኑት ወንዶች ሲሆኑ ሴቶች ደግሞ  የቀረውን 2 ሺህ 408 ቁጥር እንደሚይዙ ባህሩ ይድነቃቸው ዘግቧል።
http://www.fanabc.com/Story.aspx?ID=25767&K=

Comments

Post a Comment

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር